የሚድያው ዋና ሃሳብ ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔር ነጻነት ለማክበር በሚል የተተከለው ሥርዓት በአወቃቀርም ሆነ በአፈጻጸም የሚሊዮኖችን የብሔር ነጻነት የማያከብር መሆኑን ለማስተማር ነው። የተተከለው ሥርዓት ከነጉድለቶቹም ቢሆን እቆማለሁ የሚልለት ዓላማ በትክክል ቢተገበር እንኳን መብታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚነፍጋቸው ሚሊዮናት ኢትዮጵያውያን አሉ። ወደፊትም ይኖራሉ። እነዚህም ከሁለትና ከዚያም በላይ ከሆኑ ብሔሮች የተወለዱ ዜጎች (ውሕድ ማንነት ያላቸው) በአንድ በኩል በሌላ በኩል …
Category: Articles
🔵⚪ የክፍለ ሃገር እና የክልል አረዳድ ብዥታ⚪🔵
#ውድ የውሕድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ? • ከ1940ዎቹ ጀምረን ስናይ ሁለት የኢትዮጵያ ካርታዎች ጎልተው የታያሉ አንደኛው የቦታን ስም መሰረት ያደረገ 14 ጠቅላይ ግዛት ወይንም ክፍለ ሃገር ያለው ካርታ ሲሆን ሌላው ደግሞ ዘርን ወይንም ቋንቋን መሰረት ያደረገ 9 ክልሎች እና 2 ከተሞች ያሉት ካርታ ነው። • የዚህ ውይይት ተሳታፊዎች ስለ ካርታው ላይ ባላቸው አረዳድ በ3 ይከፈላሉ። …
⚪🔵መስሎ መኖር ከእራስ እውነታ ጋር ሲጣረስ🔵⚪
ይህንን ጽሁፍ ስናነብ ውሕድ ማንነታቸውን በአግባቡ ተቀብለውት ለዘመናት በአብሮነት ሃገራቸውን የመሩ ፣ ለሃገራቸው ህልውናና ፍቅር እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ እና እኛን የወለዱ የምንኮራባቸው ጀግኖች ቀደምቶቻችንን ሁል ግዜ ክብራቸው ክብራችን ጉድለታቸው ጉድለታችን ብለን ተቀብለን መሆኑ እንዳይዘነጋ። መስሎ መኖር ከእራስ እውነታ ጋር ሲጣረስ ሊያመጣ የሚችለው ውጤት ምን እንደሚሆን ገምተውት ያውቃሉ? ሰዎች በውሕድነታችው ምክንያት ሊወያዩባቸው የሚችሉት ጉዳዮች በርካታ ቢሆኑም …
May those with singular heritage raise their hand. ክፍል 2
በወጥ ማንነት መኖር ላይ ያለ ጥያቄ። ክፍል ሁለት። የድብልቅ ማንነት እውነታ። ባለፉት ውይይቶች ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው ውሕድ ማንነት እንዳለን እና እንዴት አብዛኛው የአንድ ዘር ማንነት አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ራቅ ስላሉት የዘር ቀደምቶቹ ያለው እውቀት እጅግ ያልተሟላ እንደሆነ ተወያይተናል። የተሟላ መረጃ አለኝ የሚሉ እና እስከ ስድስትና ሰባት ትውልድ የሚቆጥሩ እንኳን ከቀደምቶቻቸው ከ5% በታች ብቻ እንደሚጠሩ አይተናል። …
የውሕድ ማንነት እውነታ/በወጥ ማንነት መኖር ላይ ያለ ጥያቄ/ የክልል ሥርዓት በውሕድ ማንነት ላይ የደቀነው አደጋ። ክፍል 1
እጃችሁን አውጡ (May those with a singlular heritage stand up) ዉሑድ መሆናችሁ እንዲጣራላችሁ እስኪ እጃችሁ ይውጣ ውሕድ ያልሆናችሁ በእናት ባባታችሁ ምንም ሳታስቀሩ እስኪ ስምንት ቤት ዘር ሐረግ ቁጠሩ እሺ ስምንት ይቅር በጣምም አትልፉ እስከ ምንዝላቶች የወንድ የሴት ጻፉ በሉ ይቺን ቁጥር ባንድ ላይ እንያት የእናት ያባታችሁ አራት አራት አያት የአራት አያቶች አስራ ስድስት አያት የእኒህ …