Category: Art & Music
የቱ ነው ብሄሬ? የትኛውን ነው ገንጥዬ የማወጣው? መቅደስ ጸጋዬ
ብሔርንም በተመለከተ ያልተዛመድኩት ብሔር የለኝም!!..የኔ ቤተሰብ ውስጥ ሁሌም ትንሿን ኢትዮጵያዬን ነው የማየው። ለዚህ ነው እኔ እራሴን አንድ ጥግ ውስጥ ላስቀምጥሽ ብላት ማንነቴ የማትፈቅድልኝ!!..ሁሌም” #እኔ_የማውቀው_መጀመሪያ_ሰው_መሆኔን_ሲቀጥል_ ኢትዮጵያዊ_መሆኔን_ብቻ_ነው!!” የምለው፤ ይህንን ሕብር ማንነቴን ጠቅልሎ የሚገልጽልኝ #ሰውነት እና #ኢትዮጵያዊነት ብቻ ስለሆነ ነው!!! አምላካችን ሀገራችንን በምህረቱ ይጎብኝልን!!
Getish Mamo
የብዙ ሚሊዮኖች ውሕድ ኢትዮጵያንን ስሜት የሚገልጽ ዘፈን በጌትሽ ማሞ ታማኙ አያቴ ከመንዝ ተንስቶ በቾ ተቀመጠ ኦሮሞዋን አግብቶ ከዛች ከኦሮሞ ሁለት ይወልድና እነሱም ላቅም አዳም ሲደርሱ እንድገና የሶዶ ጉራጌ ሴትዋም ታገባና ከትግሬ ተጋብቶ ወንዱም ወለደ እና ከነዛ ልጆቹ እኔም ነኝ አንዱ ሁሉም ሰው ይለኛል ጌትዬ ዘመዱ እስኪ እኔን ፍረዱኝ ዘሬ ምን ሊባል ነው ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ …