Category: Literature
እናትህ በአንተ ማንነት ውስጥ ቦታ የላትም ? እጩ ዶክተር ቴውድሮስ ዘውዱ
የህገ መንግስቱ ክፍተት ውሕድ ኢትዮጵያንን አለማካተቱ ነው
⚪🔵⚪ ውሕድነትን ማወቅ … የሃገር አንድነት ብርሃን ነው!⚪🔵⚪
በሚሊዮኖች የምንቆጠር ከአንድ ብሄር በላይ የትውልድ ሃረግ ያለን ውሕድ ኢትዮጵያዊያን ለሃገራችን የአንድነት ብርሃን ነን። አኩሪ ማነታችንን አጉልተን እናውጣው። #ኢትዮጵያ ሃገራችን፦ 👉🏿 ታላቅነቷ ዳግም ይበራ ዘንድ ፣ 👉🏿 ከፍ ከፍ ብላ ትታይ ዘንድ ፣ 👉🏿 ኃይሏ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ፣ 👉🏿 ማንነቷ በአለም ይገን ዘንድ ፣ 👉🏿 ህዝቦቿ ዳግም ይኮሩ ዘንድ ፣ 👉🏿 ልጆቿ የስደት …
ሸማው ልቤ
ያባቴ ዘር ድሩ የእናቴ ዘር ማጉ በሸማኔው ታሪክ እኔን ሲደረጉ ድርን የኔ ብዬ ማግን እንዴት ልተው እኔነት ሸማዬን እየመሠረተው? ማግን የኔ ብዬስ ድርን እንዴት ልጥላ? በርሱም አይደለ ወይ የሆንኩት ነጠላ! ያለማግ ሸማ አልሆን ያለድርም ኩታ ለድርም ለማግም አለኝ ከበሬታ ድር ነኝ በይ! ማግ ነኝ በይ! የሚለው ጉተታ በሸማው ልቤ ውስጥ አይኖረውም ቦታ። by Ze’ab Alube …
ሕብሩ ጉራማይሌ
ቀይ ነሽ? ጥቁር ነሽ? ለምትሉኝ ሁሌ ጠይም ነው ቀለሜ ሕብሩ ጉራማይሌ። ያባት ዘር ድር ማጌ የናት ዘር ፈትሌ ዉሑድ ነው ሸማዬ ክሩ ጉራማይሌ። ልለያየው ካልኩኝ ድርማጉን በትኜ ልብስ አልቦ እቀራለሁ እራቁቴን ሆኜ። ላሎ ላሎ ብትል ወይም ላሌ ላሌ በሰማንያ ቋንቋ ከመረብ ገናሌ ዉሑድ ነው ያንተ ደም ምንጩ ጉራማይሌ። አሃይ ላሎ! ብትል ወይም አሃይ ላሌ! በሰማንያ …
ዉሑድ ጉራማይሌ
ገራሚ ግጥም እንጋብዛችሁ … ባባቴ ጎጃሜ በናቴ ሰላሌ ዉሑድ ነው የኔ ደም – ምንጩ ጉራማይሌ። በናቴ አገር ጅሩ – ያባቴ አበርገሌ ዉሑድ ነው የኔ ደም ምንጩ ጉራማይሌ። ባባቴ ሥልጤ ነኝ በናቴ አንጎለሌ ዉሑድ ነው የኔ ደም ምንጩ ጉራማይሌ። የናቴ አገር ጋሞ ያባቴ ሞላሌ ዉሑድ ነው የኔ ደም ምንጩ ጉራማይሌ። ያባቴ ወንዝ አባይ የናቴ ሸበሌ ዉሑድ …