Literature

ሸማው ልቤ

ያባቴ ዘር ድሩ
የእናቴ ዘር ማጉ
በሸማኔው ታሪክ
እኔን ሲደረጉ
ድርን የኔ ብዬ
ማግን እንዴት ልተው
እኔነት ሸማዬን
እየመሠረተው?
ማግን የኔ ብዬስ
ድርን እንዴት ልጥላ?
በርሱም አይደለ ወይ
የሆንኩት ነጠላ!
ያለማግ ሸማ አልሆን ያለድርም ኩታ
ለድርም ለማግም አለኝ ከበሬታ
ድር ነኝ በይ! ማግ ነኝ በይ!
የሚለው ጉተታ
በሸማው ልቤ ውስጥ አይኖረውም ቦታ።
by Ze’ab Alube
የእናንተስ ?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *