Literature

ሕብሩ ጉራማይሌ

ቀይ ነሽ? ጥቁር ነሽ? ለምትሉኝ ሁሌ
ጠይም ነው ቀለሜ ሕብሩ ጉራማይሌ።
ያባት ዘር ድር ማጌ የናት ዘር ፈትሌ
ዉሑድ ነው ሸማዬ ክሩ ጉራማይሌ።
ልለያየው ካልኩኝ ድርማጉን በትኜ
ልብስ አልቦ እቀራለሁ እራቁቴን ሆኜ።
ላሎ ላሎ ብትል ወይም ላሌ ላሌ
በሰማንያ ቋንቋ ከመረብ ገናሌ
ዉሑድ ነው ያንተ ደም ምንጩ ጉራማይሌ።
አሃይ ላሎ! ብትል ወይም አሃይ ላሌ!
በሰማንያ ቋንቋ ከራማ ሞያሌ
ዉሑድ ነው ያንተ ደም ምንጩ ጉራማይሌ።
የናትህን ቋንቋ /ያባትህን ይዘህ /ዘሬ እንዲህ ነው እያልክ/ ስታወራ ሁሌ
ቋንቋ በእድገት እንጂ/ በደም አይገኝም /ዘርህ ግን ዉሑድ ነው/ ምንጩ ጉራማይሌ።
የናትሽን ቋንቋ /ያባትሽን ይዘሽ /ዘሬ እንዲህ ነው እያልሽ/
ስታወሪ ሁሌ
ቋንቋ በእድገት እንጂ/ በደም አይገኝም /ዘርሽ ግን ዉሑድ ነው/ ምንጩ ጉራማይሌ።
ልጅስ?
የኔ አገር ደምበጫ የሚስቴ ባቢሌ
ዉሑድ ነው ልጃችን እኛ ጉራማይሌ።
እኔ ከሻምቡ ነኝ ከሶዶ ነው ባሌ
ዉሑድ ነው ልጃችን እኛ ጉራማይሌ።
ሻምቡ ነህ! ሶዶ ነህ! ብለን ብንጨቁነው
ዘሩ ጉራማይሌ ደሙ ግን ዉሑድ ነው።
እናንተስ ❓
የግጥሙ ፀሃፊ ፦
© Be Ab / Ze La

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *