Literature

⚪🔵⚪ ውሕድነትን ማወቅ … የሃገር አንድነት ብርሃን ነው!⚪🔵⚪

በሚሊዮኖች የምንቆጠር ከአንድ ብሄር በላይ የትውልድ ሃረግ ያለን ውሕድ ኢትዮጵያዊያን ለሃገራችን የአንድነት ብርሃን ነን። አኩሪ ማነታችንን አጉልተን እናውጣው።
#ኢትዮጵያ ሃገራችን፦
👉🏿 ታላቅነቷ ዳግም ይበራ ዘንድ ፣
👉🏿 ከፍ ከፍ ብላ ትታይ ዘንድ ፣
👉🏿 ኃይሏ እንደ ንስር ይታደስ ዘንድ ፣
👉🏿 ማንነቷ በአለም ይገን ዘንድ ፣
👉🏿 ህዝቦቿ ዳግም ይኮሩ ዘንድ ፣
👉🏿 ልጆቿ የስደት መከራቸው ያበቃ ዘንድ ፣
👉🏿 የድህነት ታሪኳ ያከትም ዘንድ ፣
👉🏿 የተመሰቃቀለው መስመር ይጠራ ዘንድ ፣
👉🏿 ካስማዋ ይጠብቅ ዘንድ እና
👉🏿 ብሄራዊ አንድነቷ ይፀና ዘንድ ከሚያስፈልጉ አብይ መፍትሔዎች መሃል አንዱ ሃገራዊ ማንነትን መገንባት ነው።
✔ ሃገራዊ ማንነት ለመገንባት እና የብሄር ፖለቲካ የፈጠረውን ሃገራዊ ቀውስ ለመግታት ትልቁ መድሃኒት ህዝባች ውሕድ ማንነታቸውን እንዲረዱ እና በዚህም ስብጥራዊ ማንነት የተሻለ ህብረት ፈጥረው አብሮነታቸውን እንዲጠብቁ ማንቃት ያስፈልጋል።
✔ ሃገር እንድታድግ ዜጎች ማንነታቸውን በውል አውቀውና ስብጥራዊ ውሕድነታቸውን ተረድተው እንዲነሱ ማድረግ የነገ የማይባል ስራ ነው። አሊያ አሁን ያለው ጉዞ የሆነ ወቅት ላይ ኢትዮጵያን እንደ አንባሻ እንደማይቆራርሳት እርግጠኛ መሆን አንችልም።
👉🏿 ውድ የውሕድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች በዚህ ጥልቅ ግጥም ፅሁፋችንን እናብቃ …
ጉራጌ ነኝ አትበል – ከትግራይ ነህና
ሶማሌ ነኝ አትበል – ከአፋር ነህና
ጋምቤላ ነኝ አትበል – ከስልጤ ነህና
ሲዳማ ነኝ አትበል – ከደቡብ ነህና
ኦሮሞ ነኝ አትበል – አማራ ነህና
ማንነትህ ቢታይ – በዘር ላብራቶሪ
በአንድ የዘር ሃረግ – ማንም የለም ቀሪ
በቃ …
በአዳምና ሄዋና – ባፈር ተከሽነህ
በታላቁ መዳፍ – እስትንፋስ ታድለህ
ዝቅ ስትል ውሕድ – ከፍ ስትል ሰው ነህ!
© ናቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *