የብዙ ሚሊዮኖች ውሕድ ኢትዮጵያንን ስሜት የሚገልጽ ዘፈን በጌትሽ ማሞ
ታማኙ አያቴ ከመንዝ ተንስቶ
በቾ ተቀመጠ ኦሮሞዋን አግብቶ
ከዛች ከኦሮሞ ሁለት ይወልድና
እነሱም ላቅም አዳም ሲደርሱ እንድገና
የሶዶ ጉራጌ ሴትዋም ታገባና
ከትግሬ ተጋብቶ ወንዱም ወለደ እና
ከነዛ ልጆቹ እኔም ነኝ አንዱ
ሁሉም ሰው ይለኛል ጌትዬ ዘመዱ
እስኪ እኔን ፍረዱኝ ዘሬ ምን ሊባል ነው
ዘሬን አትጠይቁኝ ዘሬ ኢትዮጵያዊ ነው
