#ውድ የውሕድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች እንደምን ሰነበታችሁ?
• ከ1940ዎቹ ጀምረን ስናይ ሁለት የኢትዮጵያ ካርታዎች ጎልተው የታያሉ አንደኛው የቦታን ስም መሰረት ያደረገ 14 ጠቅላይ ግዛት ወይንም ክፍለ ሃገር ያለው ካርታ ሲሆን ሌላው ደግሞ ዘርን ወይንም ቋንቋን መሰረት ያደረገ 9 ክልሎች እና 2 ከተሞች ያሉት ካርታ ነው።
• የዚህ ውይይት ተሳታፊዎች ስለ ካርታው ላይ ባላቸው አረዳድ በ3 ይከፈላሉ።
1. በሁለቱንም የካርታ ዘመን የኖሩ
2. ክልል ከተመሰረተ የተወለዱ
3. በክፍለ ሃገር ዘመን ከሃገር የወጡ ክልል የማያውቁ
ወደ ፊት በዚህ እርስ እስከምንመለስ ድረስ ለዛሬው በነዚህ ሃሳቦች የራስዎን ምርምር እንዲያደርጉ ጋብዘኖታል።
#እስኪ ሃሳብዎን ያካፍሉን
➣ ከክፍለ ሃገር እና ከክልል ለውሕድ የሚያመቸው የትኛው ነው?
➣ 84+ ብሄሮች ባሉበት ሃገር ከ13 ክፍለ ሃገር ወደ 9 ክልል መቀነስ ለብሄር እኩልነት መፍትሄ ይሆናል ወይ?
➣ በብሄሩ ስም ክልል የተሰጠው ብሄር አባራሪ 84+ ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ ተባባሪ የሚሆኑበት ግዜ ይታያል። ይህ የአባራሪና የተባራሪ ክስተቶች በክፍለ ሃገር ዘመን ምን ይመስሉ ነበር?
➣ ሁሉም ክልሎች የራሳቸው ህገመንግስት እንዳላቸው ያውቃሉ? የትኛው የክልል ህግ ውሕድ ማንነት ያላቸውን በተለጣፊ/በታቃፊ ሳይሆን በሙሉ የሃገር ባለቤትነት በኩልነት ይቀበለዋል።
#ሁልግዜም እንደምንለው የኢትዮጵያ ማገር የሆነውን አኩሪ ውሕድ ማንነታችንን አጉልተን እናውጣው።
#ውሕድነት እውቅና ያገኘ ማንነት ነው።
#በህዝብ ቆጠራ ወቅት ወላጆቻቸው ከአንድ ብሄር በላይ የሆኑ የሚል ምርጫ እንዳለ አይርሱ።
√ በ2007 36,524 በ1984 32,021 ውሕዶች በህዝብ ቆጠራው ተመዝግበዋል።በተለያየ ምክንያት ቁጥሩ አነስተኛ ቢሆንም 84+ ብሄር መካከል በህዝብ ብዛት 40ኛውን ቦታ ይዞ ይገኛል።
https://www.abyssinialaw.com/Ethiopian Federal and Kilil Constitutions online-resources/state-constitutions
