Video

🔵 ውሕድነት መንፈስ ነውን? 🔵

ውሕድ ማንነት እንደ ሻንጣ እየቀያየርን ተሸክመነው የምንዞረው አይደለም
ውድ የውሕድ ቤተሰቦች
ሰላምታችን ይድረሳችሁ
ጋዜጠኛ ሽመልስ ታደሰ በአባይ ሚዲያ እንግዳችን በሚለው ዝግጅቱ ላይ ከእጩ ዶክተር አቶ ቶውድሮስ ዘውዱ ጋር የነበራቸውን ውይይት ይመልከቱ ፦
የጋዜጠኛ ሽመልስ ታደሰ ጥያቄ፦
➡️ ” አንድ ሰው በ(mixed) ማንነት ወይም የተደባለቀ ማንነት አለው ፤ በአንድ ግዜ ሁሉም ባታ ሊገኝ አይችልም ፤ በአንድ ግዜ ሁሉም ቦታ ሊሰለፍ አይችልም ፤ ስለዚህ በብሄር ተሰለፍ ከተባለ ብሄሬ ይሄ ነው ብሎ ካመነ በዛ ብሄሬ ሊሰለፍ ይችላል ፤ በቋንቋ ተሰለፍ ከተባለ እንደዛው ፤ ወይም ደግሞ በሌላ በስነ ልቦና የሚዳኝም ካለ የዚህ አይነት ስነ ልቦና ነው ያለኝ ካለ እና እዚህ ነኝ ካለ በዚያ ሊሰለፍ ይችላል ፤ ሁሉም ባታ ባንዴም መገኘት አይችልም ፤ unless መንፈስ ካልሆነ በስተቀር ሰው እንደ ሰው አንድ ቦታ ነው ሊሆን የሚችለው ። ” በሚል ጋዜጠኛው እርስ በእርሱ የሚጋጭ የሚጣረስ ሃሳብ አስቀምጣል። የግለሰብ ማንነትን በቡድን ማንነት በሚጨፈልቅ ስርዓት ውስጥ አንዱን ማንነት መርጠህ ተሰለፍ እራስህን መሆን አትችልም የሚለውን ሃሳብ ማንሳት አዲስ ነገር አይደለም።

#ከብዙ ብሄረሰብ ተወልዶ ፤ በርካታ ቋንቋዎችን የሚናገር ፤ በርካታ የባህል ልብሶችና መገለጫዎች ያለው ፤ ብሄሬ ኢትዮጵያዊ ነው ፤ የምንል ውሕድ ኢትዮጵያዊ ማንነት ከምርጫዎቹ ውስጥ እንዴት አልገባም ?

#እንደ ሚዲያ እና እንደ ጋዜጠኛ ከ30 ሚሊየን በላይ የሆነውን ውሕድ ኢትዮጵያዊያንን ከመንፈስ ጋር ከማመሳሰል በፊት ጠለቅ ያለ ምርምር ማድረጉ ተገቢ ይመስለናል። የጎሳ ጽንፈኝነት ፖለቲካ በከረረ ቁጥር ከሁለቱም ወገን ሙሉ ተቀባይነት የማያገኙ ውሕድ ኢትዮጵያዊያን የመጀመሪያ ግንባር ቀደም ተጎጂዎች መሆናቸው ትኩረት ሊያገኝ ይገባል።

#ሁል ግዜም እንደምንለው በታሪክ ክስተቶች የተፈጠረውን በ30 ሚሊዮኖች በላይ የምንጋራውን አኩሪ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነውን ውሕድ ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን አጉልተን እናውጣው።

ቸር ይግጠመን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *