ውድ የውሕድ ቤተሰቦች
እንደምን ሰነበታችሁ
ዛሬ በውሕድ ማንነትን ላይ ጥናት ከሚያደርገው እጩ- ዶክተር ቴውድሮስ ዘውዱ ጋር በየኔታ ቱብ የተደረገውን ውይይት እናጋራችሁ። ብዙ ነጥቦች ተነስተዋል ፤
🔶️ አንድ ውሕድን የእናትህ ወይም የአባትህ ቋንቋ አንዱን ብቻ በመምረጥ ማንነትህ ተሰንጥቆ በነጠላ ማንነት ላይ ቁም ማለት የሰብአዊ መብቱን መንጠቅ ነው
🔶️ በስብሰባ ላይ ነጠላ ማንነትን ስብስብ የእኔ ነው ብሎ ወክሎ ይካፈል የነበረው ውሕድ ግለሰብ ስለ አጋጠመው መገለል።
🔶️የሚመረጠው ሃሳብ ሰው በራሱ እንደ ችሎታው እና ምርጫው ተገቢውን ቦታ ማግኘት አለበት የሚለው ነው። ሆኖም አሁን ባለው ሁኔታ ለነጠላ ማንነት ቦታ እንደ ተሰጠው ለውሕድም ተመጣጣኝ ቦታ ሊሰጠው ይገባል።
️ኢትዮጵያ ባለፉት ሺህ ዓመታት ባስተናገደችው በርካታ የታሪክ ክስተቶች ከ30 ሚሊዮን በላይ በኢትዮጵያዊነት ብቻ ሊገለጽ የሚችሉ ውሕድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች አፍርታለች።
ሁል ግዜ እንደምንለው የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆነውን አኩሪ ውሕድ ማንነታችንን አጉልተን እናውጣው። እኛም እንረዳው ፣ ተረድተንም ለሌሎች እናስረዳው።