Video

ውሕድ ማንነትን አልቀበለውም ፤ አንዱን ብሄር ምረጡ – ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ

ውድ የውሕድ ቤተሰቦች
በብዙ ሚሊዮኖች የምንጋራውን ውሕድ ኢትዮጽያዊ ማንነታችንን አጉልተን በማውጣት በማንኛውም ሃገራዊ ገዳዮች ላይ ነጠላ ማንነት ካላቸው ወገኖቻችን ጋር በአንድነት ለሃገር ያደረግነውን አስተዋጾ እንዲታወቅና በአንድ ብሄር በጓ ፈቃድ በታቃፊነት ሳይሆን በሃገራችን ላይ በሙሉ ባለቤትነት መኖር እንደሚገባን ስንወያይ ቆይተናል።

ውሕድ ኢትዮጵያዊነት በትውልድ የታደልነው ከሰው ሰራሸ የዘር ክልል በላይ የሆነ ኢትዮጵያን ከምስራቅ እስከ ምእራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ያካለለ ማንነት ነው።
ከ30 ሚሊዮን (አንድ ሶስተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ) በላይ ውሕዶች በታሪክ አጋጣሚዎች ተፈጥረን በሃገር ውስጥ እንዳለን ማሳወቃችንን እንዳይዘነጋ። አንድ ሶስተኛውን ህዝብ ያላካተተ ውይይት እና ሃገር ግንባታ ረዥም ጉዦ ስለማይሄድ በዚህ ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችን በንቃት ልንከታተላቸው ይገባል።
ለዛሬው ይህንን ጋብዘኖታል። ተመልክተው የእራሶን ግንዛቤ ይውሰዱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *